Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።

በሶስተኛው ምድብ የተወዳደረችው አትሌቷ ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ነው ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለችው።

በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው አትሌት ሳሮን በርሄ 9ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አልቻለችም።

የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በነገው ዕለት ከቀኑ 9 ሰዓት ከ5 ላይ ይደረጋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.