Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር የነሀስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በውድድሩ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ለሀገሯ የነሀስ ሜዳሊያ አምጥታለች።

በውድድሩ ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼቤት ቀዳሚ ስትሆን ጣሊያናዊቷ ናዲያ ባቶቼሌቲ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

ሌሎች ኢትዮጵያን ወክለው በውድድሩ የተሳተፉት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ አምስተኛ፣ አትሌት ፎትየን ተስፋይ ሰባተኛ እንዲሁም አትሌት ጽጌ ገብረሰላማ 22ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.