የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ፋውንዴሽን ተመሰረተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ራዕይን ለማስቀጠልና ለህብረተሰብ የሚጠቅሙ ተግባራትን ለማከናወን የሚረዳ ፋውንዴሽን በስማቸው ተመስርቷል።
የፋውንዴሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ሃብታሙ ወንድሙ (ፕ/ር) በምስረታ ወቅት እንዳሉት፤ በፋውንዴሽኑ የተለያዩ የምርምር ሥራዎች ይከናወናሉ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ለየት ያለ ሰብዕና ባለቤት ከነበሩት በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) የስራ ውጤት ብዙ በመማር ትውልድን መቅረፅ ይገባል ብለዋል።
የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ባለቤት እና የፋውንዴሽኑ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ትሁን ወልዴ፤ የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ራዕይን ለማስቀጠልና ለህብረተሰብ የሚጠቅሙ ተግባራትን ለማከናወን የድጋፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ፋውንዴሽኑ ጤና ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ምርምሮን እንደሚያከናውን፣ ዲጂታል ቤተ መፅሐፍት እንደሚገነባ፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ፉክክር እንዲኖርሠ፣ ወጣቶችንና ህፃናትን ለማሰልጠን እንዲሁም የፖሊሲ ግብዓቶችን ለማቅረብ ማቀዱን ጠቁመዋል።
ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ስራውን መጀመሩ ተነግሯል።
በየሻምበል ምህረት