Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ የመላ ኢትዮጵያውያን የትጋት እና የጽናት ውጤት ነው – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያውያን የትጋት እና የጽናት ውጤት ነው አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን።

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት በአሶሳ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበት የትጋትና የጽናት ውጤት ነው።

ግድቡ ለስኬት የበቃው በርካታ ፈተናዎችን አልፎ መሆኑን ገልጸው÷ ፕሮጀክቱ እውን የሆነው በሕዝቡ ድጋፍና በመንግሥት ቁርጠኛ አመራር መሆኑን ተናግረዋል።

ግድቡ ኢትዮጵያዊያን በዓባይ ጉዳይ ላይ ከታሪክ ሰሚነት ወደ ታሪክ ሰሪነት የተሸጋገርንበትና በፈተና ውስጥ የተገኘ የትውልድ አሻራ ነው ሲሉም አውስተዋል።

የክልሉ ሕብረተሰብ ከግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ይህም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የሚያስችል ስኬት ነው ብለዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.