በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ መንትዮች…
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንትዮቹ ተማሪዎች ያብጸጋ አስቻለው እና ያብተስፋ አስቻለው ይባላሉ፡፡
ተማሪዎቹ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚገኘው ሶዶ ቡኢ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ናቸው፡፡
መንትዮቹ ከልጅነታቸው ጀምሮ ተለያይተው የማያውቁ ሲሆን÷ በትምህርት ቤትም ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ሳይነጣጠሉ በተመሳሳይ ክፍል ነው የተማሩት፡፡
ይህንን ለማስቀጠልም ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አሰራር መሰረት በአንድ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ዶርም ውስጥ ተመድበው ትምህርታቸውን ለመከታተል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የቡኢ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አርጋው ወልዴ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷መንትዮቹ ለትምህርት ልዩ ዝንባሌ ያላቸውና በየዓመቱ ከክፍላቸው ጥሩ ውጤት የሚያስመዘግቡ የደረጃ ተማሪዎች ናቸው፡፡
በመልካም ሥነ ምግባራቸው በማሕበረሰቡ ዘንድ የተመሰከረላቸው እንደሆኑ እና በትምህርታቸውም ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተጠባቂ ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በ12ኛ ክልፍ ሀገር አቀፍ ፈተናም ተቀራራቢ የሆነ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከትምህርት ቤታቸው አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን ማለፋቸውን ነው ያስረዱት፡፡
በዚህ መሰረትም ተማሪ ያብጸጋ አስቻለው ከ600ው በአጠቃላይ 548 ያመጣ ሲሆን÷ ተማሪ ያብተስፋ አስቻለው ደግሞ 543 አስመዝግቧል፡፡
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!