የሕዳሴ ግድብ ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ሊደረግ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ከሰኞ ጀምሮ ምዝገባ በማድረግ መጎብኘት ይቻላል አሉ።
ሚኒስትሯ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪስት መስህቦችን ጎብኝተዋል።
በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ጎብኝዎች ሕዳሴ ግድብን በአንድ ጊዜ 50 በመሆን መጎብኘት ይችላሉ።
ምዝገባው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል እንደሚሆን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡