Fana: At a Speed of Life!

የተቀበላችሁት ሹመት የሠራዊቱን ቀጣይነት ያለው ግንባታ ያሳያል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ የተቀበላችሁት ሹመት የሠራዊቱን ቀጣይነት ያለው ግንባታ ያሳያል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ኢትዮጵያ የሾመቻችሁ የመከላከያ የጦር መኮንኖች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ውትድርና በመሥዋዕትነት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰው፤ ሕይወት ከመስጠት የበለጠ ስጦታ የለም ሲሉ ገልጸዋል።

ዛሬ የተቀበላችሁት ሹመት የሠራዊቱን ቀጣይነት ያለው ግንባታ፣ የኢትዮጵያን ማኅፀነ ለምለምነት፣ የእናንተንም ትጋት ያሳያል ብለዋል።

የጦር መኮንኖቹ በቀጣይ አገልግሎታቸው ሠራዊቱን የበለጠ በማዘመን በአቋምና በዐቅም የላቀ እንደሚያደርጉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም የጦር መኮንኖችን መሾማቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.