ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ወቅት ላበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው እውቅና የመስጠት መርኃ ግብር ላይ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተወጣው ሀገራዊ ኃላፊነት የልዩ እውቅና ሽልማቱን ወስዷል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በመርኃ ግብሩ ላይ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሁነቱን ተከናወነ ከሚል ተለምዷዊ አሸፋፈን ወጥተው ዘገባ ሰርተዋል።
የኢትዮጵያን የእድገት ጉዞ በሚገባ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጉባኤው በስኬት የመጠናቀቁ አንዱ ምክንያት መገናኛ ብዙኃን ሥራቸውን በባለቤትነት በመሥራታቸው ነው ብለዋል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የመንግስትና የግል የመገናኛ ብዙኃንም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።