በድሬዳዋ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የድሬ-መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ።
መርሐ ግብሩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ እና የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በተገኙበት ነው የተካሄደው።
እናትዓለም መለሰ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ማዕከሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ስብራትን ከመሰረቱ የሚቀይር ትልቅ እመርታ ነው።
መሶብ በብቁ የሰው ኃይል የተደራጀ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ዘመኑን የዋጀ የከተሞቻችን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚመጥን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም የዳበረ ተባብሮ የመኖር እና በጋራ የመስራት ባህል በመጠቀም ተቋሙን የሕዝብ እርዳታ መፍለቂያ ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው÷ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ጊዜያት ተጨባጭ ውጤቶችን በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት አዲስ ጅማሮ ላይ ደርሰናል ብለዋል።
መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል የመንግስት ተቋማት አገልግሎትን ማሻሻል አንዱ እንደሆነ ገልጸው÷ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለመገንባት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተግባራዊ መደረጉን ጠቁመዋል።
ማዕከሉ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የማይተካ ሚና ከመጫወት ባለፈ ቀልጣፋ እና ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ ስማርት ድሬዳዋን ዕውን ለማድረግ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እንደሆነም አስረድረዋል።
ማዕከሉን የመጀመሪያ ዙር ስራዎች ለማስጀመር አስፈላጊ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ከ10 ተቋማት በተለዩ 28 አገልግሎቶች እንደሚሰጡና 64 ባለሙያዎች እና አስተባባሪዎች ተለይተው አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!