Fana: At a Speed of Life!

በሊጉ የመጀመሪያ ሣምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ቡናን ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያገናኘው ተጠባቂ ጨዋታ በመጀመሪያ ሣምንት የሚደረግ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል የአምና የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በመጀመሪያ ሣምንት ከአዳማ ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ውድድሩ በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ እና ሀዋሳ ከተሞች እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

የመጀመሪያውን ዙር ውድድር በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተማ ላይ ለማድረግ መታቀዱን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

ምድብ አንድ ላይ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ፋሲል ከነማ፣ ሽረ ምድረ ገነት፣ መቻል፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና ተደልድለዋል፡፡

ነጌሌ አርሲ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ባሕር ዳር ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ሸገር ከተማ፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ምድብ ሁለት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሁለት ምድቦች ተከፍሎ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.