ማንቼስተር ዩናይትድ በብሬንትፎርድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወደ ለንደን ያቀናው ማንቼስተር ዩናይትድ በብሬንትፎርድ 3 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች ኢጎር ቲያጎ (2) እና ማቲያስ የንሰን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የማንቼስተር ዩናይትድን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ ቤንጃሚን ሼሽኮ አስቆጥሯል፡፡