ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ግራሃም ፖተርን ያሰናበተው የለንደኑ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶን ሾሟል፡፡
በቅርቡ ከኖቲንግሃም ፎረስት የተሰናበተው ኑኖ የሶስት ዓመት ኮንትራት ለዌስትሃም ዩናይትድ መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ በሦስት ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ ፥ ከወዲሁ ከካራባኦ ዋንጫ ውጭ ሆኗል፡፡