ኢሬቻን በድምቀት ለማክበር ተዘጋጅተናል – አባ ገዳዎች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮውን ኢሬቻ ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በልዩ ድምቀት ለማክበር ተዘጋጅተናል አሉ አባ ገዳዎች።
አባ ገዳ ግርማ በቀለ ኢሬቻ በክረምት ወቅት በነበረው ዝናብ የወንዝ ሙላትና ጎርፍ በመሳሰሉ ምክንያቶች የተራራቁ ቤተዘመዶችና ሕዝቡ የወንዝ ሙላቱ ቀንሶና ብርሃን ፈንጥቆ ዳግም የሚገናኙበት፣ የሚጠያየቁበትና ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበት ነው ብለዋል።
የኢሬቻ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የገዳ ሥርዓት አንዱ መገለጫ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አባ ገዳ ወልደ አብ በበኩላቸው፤ ኢሬቻ ሁሉም በጋራ የሚያከበረውና የአብሮነት መገለጫ የሆነ የምስጋና፣ የሰላምና የአንድነት በዓል መሆኑን ጠቅሰው፥ ለሕዝቦች መስተጋብር አስተዋጽኦ ያለው ነው ብለዋል።
ዘንድሮ የሚከበረው ኢሬቻ ሀገራችን ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ባስመረቀችበት ማግስት እንዲሁም በኮሪደር ልማት ሰፋፊ ስራዎች በተሰሩት ወቅት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው እና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውን አባገዳዎቹ ተናግረዋል።
ኢሬቻን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን የሚያጠናክሩ እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ናቸው።
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ለረጅም ዓመታት ጠብቆ ካቆያቸው ድንቅ የገዳ ማህበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ መሆኑን በማንሳት፥ የፍቅርና የአብሮነት መገለጫ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።
ኢሬቻ ለቱሪዝም መስህብነት ብሎም ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰው፤ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ከትወልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ማልማትና መንከባከብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!