የተሻሻለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት…
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን ከ300 ወደ 297 ዝቅ አድርጓል፡፡
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ÷ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተማሪዎች ወደቀጣይ የትምህርት ደረጃ ለመዛወር 50 በመቶና ከዚያ በላይ ማምጣት እንዳለባቸው ይደነግጋል።
በዚህ መሰረትም በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው 49 ነጥብ 50 እስከ 49 ነጥብ 99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑን አመልክቷል፡፡
ውሳኔውን ተከትሎም 49 ነጥብ 5 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ እንዳሟሉ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ስለሆነም 49 ነጥብ 5 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!