ነፃ የንግድ ቀጣና ግብይት በኢትዮጵያ መጀመሩ መንግሥት ቃልን ወደ ተግባር የመቀየር ቀጣይ ርምጃን ያሳየ ነው – አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ግብይት በኢትዮጵያ መጀመሩ መንግሥት ቃልን ወደ ተግባር የመቀየር ቀጣይ ርምጃን ያሳየ ነው አሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ።
አቶ አደም ፋራህ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ግብይት ሥርዓት በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡
ነፃ የንግድ ቀጣናው ለአፍሪካውያን ሰፊ የንግድ ዕድል እንዲሁም የኢንቨስተሮችን የንግድ ትስስርን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ነፃ የንግድ ቀጣናውን መጀመሯ በአፍሪካ ያላትን ታሪካዊ ሚና በንግዱ ዘርፍም የደገመችበት ነው ብለዋል።
ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ተልከዋል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በቅድስት አባተ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!