የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሜዳ ለውጥ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ሊደረጉ የነበሩ የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታዎች የሜዳ ለውጥ ተደርጎባቸዋል አለ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር፡፡
የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንታት ውድድር በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ እንደሚደረግ ተገልጾ እንደነበር ማህበሩ አስታውሷል፡፡
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ድሬዳዋ ከተማ ውድድሩን ለማስተናገድ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ጨዋታውን ለማስተናገድ እንደማይችል ማሳወቁን አክሲዮን ማህበሩ ገልጿል፡፡
በመሆኑም ድሬዳዋ ላይ ሊደረጉ የነበሩ የመክፈቻ ሳምንታት ጨዋታዎች ወደ ሀዋሳ ከተማ መዞሩን ጠቅሶ፥ የተስተካከለውን መርሐ ግብር በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡