Fana: At a Speed of Life!

በጨፋ ሮቢት ከተማ በትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጨፋ ሮቢት ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው 60 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ልዩ ስሙ ጃራ ድልድይ ከተባለ ቦታ ላይ ከከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በአደጋውም እስካሁን የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የከተማው ከንቲባ አቶ ሰይድ መሃመድ ለፋና ዲጀታል ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ጠቁመው ÷ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል አመልክተዋል፡፡

በአቤል ነዋይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.