Fana: At a Speed of Life!

ሠንደቅ ዓላማችን የማንሰራራት ጉዞ ዓርማችን ነው – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሠንደቅ ዓላማችን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነታችንን የምናሳይበት የማንሰራራት ጉዞ ዓርማ ነው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ።

18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሠንደቅ ዓላማችን የብዝኃነታችን፣ የእኩልነታችንና የሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ ነው።

ቀኑ ለሠንደቅ ዓላማችን ልንሰጠው የሚገባውን ክብርና ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት እንዲሁም ብሔራዊ የአርበኝነት መንፈሳችንን የምንቀሰቅስበት ታላቅ ዕለት ነው ብለዋል።

ሠንደቅ ዓላማው የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ሊሰብሩ የማይችሉትን የሕብረ ብሔራዊ አንድነት እና የሉዓላዊነት ምሽግ እንደሆነም ገልጸዋል።

ሠንደቅ ዓላማችን ፈተናዎችን በጽናት ተሻግረን አፍሪካዊት የልማት ተምሳሌት የሆነች ሀገር የመገንባት አቅማችንን የምናጎለብትበት ብሎም ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነታችንን የምናሳይበት የማንሰራራት ጉዞ አርማ ነው ሲሉም አመላክተዋል።

ሰንደቅ ዓላማችን በታሪክ ውጣውረዶች ውስጥ የጽናታችን ምልክት ነው ያሉት አፈ ጉባኤው÷ ዛሬም ለኢትዮጵያ ብልጽግናና ዘናቂ ልማት ያለንን ጽኑ አቋም እንዲሁም ወደ ብሩህ ከፍታ ዘመን የተሻገርን መሆናችንን የምናውጅበት ነው ብለዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.