በአፍሪካ በሎጂስቲክስና ማሪታይም ዘርፍ ብቁ የሰው ሃይል ለማፍራት መስራት ይገባል – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ በሎጂስቲክስ እና ማሪታይም ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ የሰው ሃይል ለማፍራት በትብብር መስራት ይገባል አሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ።
የአፍሪካ ማሪታይም ጉባዔ የአፍሪካ ሀገራት ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሮች እንዲሁም የማሪታይም ሃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአፍሪካ በማሪታይም ዘርፍ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ዘመኑን የዋጀ የሰው ሃይል ለማፍራት በትኩረት መስራት ይገባል፡፡
ኢትዮጵያ በተለያዩ የሥልጠና ማዕከላት ብቁ ባሕረኞችን እና ሌሎች ባለሙያዎችን ለማፍራት እየሰራች እንደምትገኝ አስገንዝበዋል፡፡
ጉባዔው የአፍሪካ ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን እምቅ አቅም በመጠቀም በትብብር እንዲሰሩ እድል ይፈጥራል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡
በአፍሪካ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና አስተማማኝ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት የዘርፉ ተዋናዮች ትስስር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሎጂስቲክስ እና ማሪታይም ዘርፍ በትብብር እና በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ እንደሆነችም አረጋግጠዋል፡፡
2ኛ ቀኑን በያዘው ጉባዔው የአፍሪካ ሀገራትን የብሉ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተመላክቷል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!