ፋና 80 የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በመጪው እሑድ ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመጀመሪያው የፋና 80 የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በመጪው እሑድ ጥቅምት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት መካሄድ ይጀምራል።
በአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድሩ በፋና 80 ምዕራፍ 1፣ 2 እና 3 ድንቅ ችሎታቸውን በማሳየት ያሸነፉ እና ተፎካካሪ የነበሩ 16 ቡድኖች ይሳተፋሉ።
ለ11 ሳምንታት የሚዘልቀው ፋና 80 የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በሁለት ምድብ ተከፍሎ በመጪው እሑድ መካሄድ ሲጀምር÷በምድብ አንድ የተደለደሉ ስምንት ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ሥራቸውን ያቀርባሉ።
የምድብ አንድ ተፎካካሪዎች እናት የባህል ቡድን፣ አራት ነጥብ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ ነገስታት ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ አንድ ኢትዮጵያ የባህል ቡድን፣ ጊዮን ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ ኢትዮጵያን የባህል ቡድን፣ ሜዝ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን እና ኢትዮ ወግ የባህል ቡድን ናቸው፡፡
በሲሳይ ገብረማርያም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!