የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፉን የስኬታማ ተቋም ሽልማት አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዓለም አቀፍ የስኬታማ ተቋም ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በጣሊያን ሮም በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡
ሽልማቱ የፋኦ መርሐ ግብሮች በብቃት በመተግበር በተለይ ዘላቂ የግብርናና የገጠር ልማትን፣ የምግብ ዋስትናንና ፈጠራን በማሳደግ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማትና ግለሰቦች የሚሰጥ ዓለም አቀፍ እውቅና ነው።
ኢንስቲትዩቱ በግብርና ኤክስቴንሽን እና ምርትን ለማሳደግ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገርና ሁሉን አቀፍ የግብርና ስርዓቶችን ለማስተዋወቅና በግብርናው ዘርፍ የእውቀት ልውውጥን ለማጎልበት ባከናወናቸው ተግባራት ሽልማቱ እንደተበረከለት ተገልጿል፡፡
ሽልማቱ የተቋሙ ሰራተኞችና አጋር አካላት የትጋት ውጤት መሆኑን ገልጾ፥ በቀጣይም የአርሶ አደሮችንና የገጠር ማህበረሰቦችን ዘላቂ ልማትና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከአጋር ደርጅቶች ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጧል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!