Fana: At a Speed of Life!

ግብር ከፋዮች ለመዲናዋ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግብር ከፋዮች የሚሰበሰበው ገንዘብ ለመዲናዋ እና ለሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
የከተማ አስተዳደሩ ግብር ከፋዮች የዕውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴን ጨምሮ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በመዲናዋ የታማኝ ግብር ከፋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመሩ የሚሰበሰበው የብር መጠን ከፍ ብሏል።
ከግብር ከፋዮች የሚሰበሰበውን ገንዘብ መልሰን ለዘላቂ ልማትና ድህነትን ለመቀነስ እያዋልነው ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በየደረጃው የሚገኙ ግብር ከፋዮች የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት ለከተማዋ ልማት እያበረከሩት ላለው አተዋጽኦ አመስግነዋል።
ከንቲባዋ ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታና ስልጣኔ መሆኑ ጠቅሰው፥ ሁሉም የሚጠበቅበትን ግብር በመክፈል ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ በበኩላቸው፥ ቢሮው የአደረጃጀት፣ ቴክኖሎጂና ሪፎርም ሥራዎችን በማከናወን ሀገር የሚያስፈልጋትን ገቢ እንድታገኝ እየሰራ ይገኛል ነው ያሉት።
በበጀት አመቱ ከተማዋ ማግኘት ያለባትን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በቅድስት አባተ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.