ሀገርን ከድህነት ለማላቀቅ የግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ ነው – አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገርን ከድህነት ለማላቀቅና ልማትን ለማረጋገጥ የግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ ነው አሉ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለታማኝ ግብር ከፋዮች ያዘጋጀው የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ላይ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ መንግስት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በጥራት እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።
የፌደራል መንግሥትም ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢ የመሰብሰብ አቅማቸውን በማሳደግ የማህበረሰቡን ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
በከተሞች እድገት፣ በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ዘርፎች ለተመዘገቡት ጉልህ ስኬቶች የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚታየው ሁለንተናዊ ለውጥ ያለታማኝ ግብር ከፋዮች አስተዋጽኦ ይሳካል ተብሎ የሚታሰብ አለመሆኑን ገልጸው፥ አዲስ አበባ ከተማ እንደገና እንድትሰራ ማድረጋቸውንም አፈ ጉባኤው ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባን የአፍሪካ ከተሞች ምሳሌ እንድትሆን የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው፥ የመዲናዋ ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
ታማኝ ግብር ከፋዮች ለሀገርና ለከተማዋ ልማት ላበረከቱት አስተዋፅኦ በማመስገን፥ የግብር ከፋዩ መሰረታዊ አገልግሎትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየጊዜው እየፈተሹ መፍትሄ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!