የአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮች የዕውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግብር ከፋዮች የዕውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
በመድረኩ በከተማዋ ለሚገኙ 366 ታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር፣ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ፣ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ታማኝ ግብር ከፋዮች ተገኝተዋል።
በቅድስት አባተ