Fana: At a Speed of Life!

ዲጂታላይዝ የተደረገው የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓት…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አሰራር ሒደትን ዲጂታላይዝ ማድረግ ተችሏል አለ የጤና ሚኒስቴር፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 7ኛው ሀገር አቀፍ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ዓመታዊ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ፍሬሕይወት አበበ እንዳሉት÷ በ2017 በጀት ዓመት የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱን ለማጠናከር የሚያስችል የአዋጅ እና አሰራር ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጓል።
ማሻሻያው የተራዘመ የመድሃኒት የግዢ ሒደት ላይ ለውጥ ማምጣቱንና ከተቋማት ጋርም ውል የተገባለት አቅርቦት ሥርዓት በመፈራረም ወደ ሥራ መገባቱን አስረድተዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 68 ቢሊየን ብር የሚያወጣ መድኃኒትና ሕክምና ግብዓት መሰራጨቱን ጠቁመው÷ ከ22 ሺህ በላይ ለሆኑ የመንግስት ተቋማት ተደራሽ መደረጉን አንስተዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በበኩላቸው÷ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማዘመንና የሀገር ወስጥ አምራቾችን ለማበረታታት የሚያስችል ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡
በዚህም የሀገር ውስጥ አምራቾች ድርሻ 41 በመቶ መድረሱን ጠቁመው÷ ፈጣንና ተጠያቂነት ያለው ሥርዓት ለማጠናከር እንደሚሰራ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.