ማዕከሉ አሥተማማኝ የኮማንዶ ሃይል አሠልጥኖ እያበቃ ነው – ሌ/ጄ ሹማ አብደታ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አሥተማማኝ የኮማንዶ ሃይል አሠልጥኖ እያበቃ ነው አሉ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ፡፡
ሌ/ጄ ሹማ አብደታ በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ብላቴ በመገኘት የ4ኛ ዙር መሠረታዊ ውትድርና ስልጠናን በማስጀመር የ44ኛ ዙር የኮማንዶ ሠልጣኞችን ተመልክተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ማሰልጠኛ ት/ቤቱ በዲሲፕሊን የታነጸ ትክክለኛና ፅናትን የተላበሰ ሀገራዊ ፍቅር ያለው ኢትዮጵያዊ ሠራዊት የሚገነባበት ማዕከል ነው ብለዋል፡፡
ሠልጣኞች የአሰልጣኞችን የካበተ ልምድ በመጠቀም በዲሲፕሊን የታነጸ ጠንካራ እንዲሁም ሀገራዊ ፍቅርን የተላበሰ ወታደር ለመሆን ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ኮማንዶ በታማኝነት ራሱን አሳልፎ በመስጠት ለሀገሩ አኩሪ ታሪክ የሚሰራ መሆኑን ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ አውስተዋል፡፡
ኮማንዶ የውጊያ ማርሽ ቀያሪና የዘገዩ ውጊያዎችን የሚያፋጥን ጀግና ነው ሲሉ መግለጻቸውንም የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ሌ/ኮ ውብሸት ቸኮል ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!