Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 29ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡

መነሻውን  እና  መድረሻውን ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ባደረገው ውድድር በወንዶች አትሌት አበባው ደሳለኝ ከመቻል በቀዳሚነት በመግባት ውድድሩን ሲያሸንፍ፤ በግል የተወዳደሩት አትሌት አስራር ሀይረዲን እና ቶልቻ ተፈራ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በሴቶች ደግሞ በግል የተወዳደረችው አትሌት ረድኤት ዳንኤል በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ አትሌት ሲጫሌ ደለሳ  ከፌደራል ፓሊስ፣ አትሌት መሰረት ፍላቴ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል።

ዘንድሮ ለ29ኛ ጊዜ በተደረገው ውድድር ላይ ከክለብ እና በግል የተወዳደሩ ከ180 በላይ አትሌቶች በውድድሩ ላይ ተሳትፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት፣ የፌዴሬሽኑ አመራሮች እና የስራ አስፈፃሚ አባላት እንዲሁም የቀድሞ አንጋፋ አትሌቶች ተገኝተው ውድድሩን ተከታትለዋል።

በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ለወጡ አትሌቶች በየደረጃው የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በእንዳልካቸዉ ወዳጄ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.