Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ሲያን ዳይች የኖቲንግሃም ፎረስት አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ሲያን ዳይች የኖቲንግሃም ፎረስት አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡

አሰልጣኝ ሲያን ዳይች በኖቲንግሃም ፎረስት እሰከ ፈረንጆቹ 2027 ድረስ የሚያቆያቸውን ኮንትራት ተፈራርመዋል።

አሰልጣኝ አንጂ ፖስቴኮግሉን ተክተው የኖቲንግሃም ፎረስት አሰልጣኝ የሆኑት ዳይች ፎረስት በዩሮፓ ሊግ ከፖርቶ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ስራቸውን ይጀምራሉ፡፡

የ54 ዓመቱ አሰልጣኝ ሲያን ዳይች ከዚህ ቀደም ዋትፎርድ፣ በርንሌይ እና ኤቨርተንን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡

አንጂ ፖስቴኮግሉ ከ39 ቀናት የኖቲንግሃም ፎረስት ቆይታ በኋላ ባለፈው ቅዳሜ መሰናበታቸው አይዘነጋም፡፡

ኖቲንግሃም ፎረስት በሊጉ ካደረጋቸው 8 ጨዋታዎች 5 ነጥብ በመሰብስብ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡‎

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.