Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ትብብር…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በሞስኮ ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል የሁለቱ ሀገራት መገናኛ ብዙሃን ትብብር አንዱ ነው፡፡

ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት የሩሲያው ሚዲያ ስፑትኒክ በዘርፉ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን አድንቀዋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በበኩላቸው፥ የሚዲያው ተደራሽነት እየሰፋ መምጣቱንና የተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

እውነታን በተለያዩ ሀገራት ማድረስ ወቅቱ የሚፈልገው ወሳኝ ተግባር መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ በዚህ ረገድ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ከሁለቱ ሀገራት አዳዲስ የትብብር መስኮች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነት ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ በጋራ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.