Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከአቡዳቢ የልማት ፈንድ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከአቡዳቢ ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ሳይፍ አል ሱዋይዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለውን የቆየ አጋርነት ስለማጠናከር መክረዋል፡፡

አቶ አህመድ ሺዴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የአቡዳቢ ልማት ፈንድ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ዘላቂ ልማትና የስራ እድል ፈጠራን የሚያበረታቱ ቁልፍ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ በመደገፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ተቋማቸው የኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚ የመገንባት ጥረት ለመደገፍና የሁለቱን ሀገራት ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን በማስፋት ለጋራ ተጠቃሚነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.