በኡጋንዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ63 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኡጋንዳ ካምፓላ የጉሉ አውራ ጎዳና ላይ በደረሰው የተሽከርካሪዎች ግጭት የ63 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የሀገሪቱ ፖሊስ እንዳስታወቀው÷ አደጋው የተከሰተው በተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዙ የነበሩ ሁለት አውቶብሶች መኪና ደርበው ለመቅደም ሲሞክሩ ነው።
ከካምፓላ ወደ ጉሉ ከተማ በሚወስደው የጉሉ አውራ ጎዳና ላይ በተከሰተው አደጋ አውቶብሶቹ ተጋጭተው ሚዛናቸውን በመሳት የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰባቸው ነው ፖሊስ የገለጸው።
በአደጋው በርካቶች ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንም አመላክቷል።
አሽከሪካሪዎች ለከባድ አደጋ የሚያጋልጡ ደርቦ የማለፍ ተግባሮችን እንዲቀንሱ ያሳሰበው ፖሊስ÷ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደተጀመረ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዮናስ ጌትነት