አርሰናል ክሪስታል ፓላስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር በሜዳው ኢምሬትስ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው አርሰናል 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ምሽት 11 ሰዓት በተካሄደው በዚህ ጨዋታ አርሰናል መሪነቱን ያጠናከረበትን ብቸኛ ግብ በመጀመሪያ አጋማሽ ኤብሪቼ ኤዜ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎም አርሰናል ነጥቡን ወደ 22 ከፍ አድርጓል።
በተመሳሳይ ሰዓት ወደ ቪላ ፓርክ ያቀናው ማንቼሰተር ሲቲ በአስቶንቪላ 1 ለ 0 ሲሸነፍ ማቲ ካሽ የአስቶን ቪላ ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ ዎልቭስ በበርንሌይ 3 ለ 2 ተሸንፏል።