6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከም/ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡