Fana: At a Speed of Life!

የባሌ ህዝብ የሀገርን ሀብት ጠብቆ በማቆየቱ መመስገን አለበት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሌ ህዝብ የሀገር ሀብት የሆኑትን ብሔራዊ ፓርክና የሶፍ ኡመር ዋሻ ጠብቆ በማቆየቱ መመስገን አለበት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በዚሁ ወቅት የምክር ቤት አባል የባሌን ህዝብ በመወከል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን የምስጋና መልዕክት ተከትሎ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽ ከመንግስት ይልቅ መመስገን ያለበት የባሌ ህዝብ ነው ብለዋል፡፡

ህዝቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎትና የመንገድ መሰረተ ልማት እንኳን ባልተሟለበት ሁኔታ፥ የሀገር ሀብት የሆነውንና ከ2ሺህ ሄክታር በላይ የሚሸፍነውን ብሔራዊ ፓርክ በጀግንነት ጠብቆ በማቆየቱ አምስግነዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የባሌን ያህል ሀብት ያለውም ሆነ የባሌን ያህል ስራ ያልተሰራበት አካባቢ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ህዝቡ ያንን የሚያህል ጫካ በመጠበቁ ሊመሰገን የሚገባው አስደማሚ ህዝብ መሆኑን አውስተዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያውያን፣ የምክር ቤት አባላትና ተመራማሪዎች የሶፍ ኡመር ዋሻን እንዲጎበኙና እንዲመራመሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የሶፍ ኡመር ዋሻ ያንን ቦታ ለማራከስ ውሃ የፈጠረው ዋሻ ነው ቢባልም በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ተፈጥሮን መሰረት አድርጎ በከፍተኛ ድካም የተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ታሪክ እንደሚያመለክተው ጋር ውሃ ገድበው ነበር የሰሩት ማጣራት ይፈልጋል እንጂ ዋሻው እስከ ሱማሊያ ጨፍ የሚደርስ ነው።

ዋሻውን ሶፍ ኡመር ከህዝብ ጋር በመሆን ውሃ ገድበው የሰሩትና አዳራሽና የመስገጃ ቦታ ጭምር ያለው ሲሆን፥ የባሌ ህዝብ ይህንን ቅርስ ጠብቆ በመቆየቱ መመስገን ይገባዋል ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.