Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የቀረበለትን የድጋፍ ሞሽን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የቀረበውን የ2018 የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የድጋፍ ሞሽን አጽድቋል።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በፕሬዚዳንቱ የቀረበውን ሞሽን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተውባቸዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበለትን የድጋፍ ሞሽን በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.