Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ያሉ አካላት መንግስት የጦርነት ዓላማ እንደሌለው ተገንዝበው ወደ ሰላም ሊመጡ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል ያሉ አካላት የፌደራል መንግስት የጦርነት ዓላማ እንደሌለው በመገንዘብ ወደ ሰላም ሊመጡ ይገባል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፌደራል መንግስት ወደ ትግራይ ክልል የሚልከው በጀት ለወታደሮች እየዋለ በመሆኑ ህዝቡን እየጎዳ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ክልል ተጨማሪ ውጊያ እንደማያስፈልግ ገልጸው፥ ሕወሓት ምርጫ ቦርድና ህገ መንግስትን አክብሮ ሕጋዊ ፓርቲ በመሆን በምርጫ ተወዳድሮ መንግስት መሆን እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡

የኢትዮጵያን መንግስት በጦርነትና በኃይል ማሸነፍ ስለማይቻል ወደ ሰላማዊ ንግግር በመምጣት ተባብረን ኢትዮጵያን እናልማ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የፌደራል መንግስት ትግራይ ክልል ላይ የጦርነት ዓላማ የለውም፥ ትግራይ ክልል ያሉ አካላትም ይህንን ተገንዝበው ወደ ሰላም ሊመጡ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.