Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሞሮኮ ከምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆኗል፡፡

ከታንዛኒያ አቻው ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታውን በድሬዳዋ ስታዲየም ያደረገው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

በድምር ውጤት በታንዛኒያ አቻው 3 ለ 0 በሆነ ውጤት የተሸነፈው ብሔራዊ ቡድኑ ከ2026ቱ የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከ14 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.