ኢትዮጵያ እና ቻይና በፍትሕ ዘርፍ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ቻይና በፍትሕ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት በመተግበር ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
በፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ የተመራ ልዑክ ከነገ ጀምሮ በቻይና ጓንጁ ከተማ በሚካሄደው የቻይና-አፍሪካ የዐቃብያነ ሕግ የትብብር ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡
ሚኒስትሯ ከፎረሙ አስቀድሞ ከቻይና ሉዓላዊ ሕዝብ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዪንግ ዮንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ቻይና በፍርደኞች ማዘዋወርና በወንጀል ጉዳዮች በትብብር ለመስራት የደረሱባቸውን ስምምነቶች ለመተግበር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የሁለቱ ሐገራት የፍትሕ ሚኒስትሮች በፍትሕ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን በማስታወስ በቀጣይ በበለጠ ትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡