2ኛው ቀጣናዊ የእጽዋትና እንስሳት ጤና አጠባበቅ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛው ቀጣናዊ የእጽዋትና እንስሳት ንጽህና እና ጤና አጠባበቅ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚካሄደውን ጉባዔ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣ እና የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾችና ላኪዎች ማህበር በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡
በቀጣናው በእንስሳትና እፅዋት ንጽህና እና ጤና አጠባበቅ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እና እድሎች ቀርበው በጉባዔው ውይይት ይደረግባቸዋል።
በጉባዔው ኢትዮጵያ እፅዋትና እንስሳት ምርቶችን በተደራጀ መረጃ ለመያዝ የሚያስችል የኢፋይቶ አገልግሎት አስጀምራለች።
የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) ÷ የአገልግሎቱ መጀመር ደህንነቱ የተጠበቀ የእፅዋትና እንስሳት ምርትን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል።
ኢፋይቶ የዓለም ጤና እና ንግድ ድርጅቶች የእፅዋትና እንስሳት ምርቶችን በተመለከተ የሚያወጧቸውን መስፈርቶች ለማሟላት እንደሚያስችል አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በበኩላቸው ÷ 66 አገልግሎቶችን ኦንላይን መስጠት የሚያስችሉ ከ4 ሺህ በላይ መረጃዎችን በማቀናጀት የዲጂታል አገልግሎት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከ66 አገልግሎቶች 29 ኙን በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ውስጥ አካትቶ እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!