በሀገር ውስጥ የተመረቱ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በሙከራ የተረጋገጡና በሀገር ውስጥ የተሰሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረትም በኢትዮጵያ የመጀሪያ የሆነው ማንኛውንም ማሽነሪ ማንቀሳቀስ የሚያስችል ሞተር በኢንስቲትዩቱ ተሰርቶ ለምረቃ በቅቷል።
የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ስማርት የመንገድ ዳር መብራትን ጨምሮ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችም በዛሬው ዕለት ይፋ ሆነዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚህ ወቅት ÷ በኢትዮጵያ ከውጭ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን የሚተኩ ፈጠራዎችን በማምረት ትልቅ ውጤት እየታየ ነው ብለዋል፡፡
እነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሀገር ውስጥ ችግርን በመፍታት ሀገሪቷ ክህሎትን ለማሳደግ የጀመረችውን ግብ ለማሳካት ያስችላሉ ነው ያሉት፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የትኩረት አቅጣጫ በሆኑ ግብርና፣ ማዕድንና ኢነርጂ መስኮች የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል፡፡
መሰል ውጤቶች ዜጎች ለፈጠራ እንዲሁም ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ያላቸውን ምልከታ እንደሚያሳድጉ አስገንዝበዋል፡፡
በእየሩሳሌም አበበ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!