የተቀናጀ የውኃ ሃብት አስተዳደርን ማጠናከር…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ውኃ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት የተቀናጀ የውኃ ሃብት አስተዳደርን ማጠናከር ይገባል አለ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር።
“ውሃና ንጹህ ኢነርጂ ለዘላቂ እድገት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ውኃና ኢነርጂ ሳምንት በውኃ ሃብት ዘርፍ በተገኙ ስኬቶች፣ መሻሻል ስለሚገባቸውና ቀጣይ ርምጃዎች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ተደርገዋል።
የዕለቱን መርሐ ግብር ያስጀመሩት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አማካሪ ሞቱማ መቃሳ እንዳሉት÷ ውኃ የህልውናችንና የኢኮኖሚያችን መሰረት እንዲሁም ለብልጽግና፣ ሰላምና ልማት ወሳኝ የሆነ ስትራቴጂካዊ ሃብት ነው።
በጣም ተጋላጭ፣ አከራካሪ እና ዓለም አቀፍ ስጋቶች ሁሉ በውኃ ላይ ትኩረት ማድረጋቸው ለዘላቂ ልማትና ለሰብዓዊ ደህንነት ማዕከላዊ እንደሚያደርገውም አንስተዋል።
ውድ የሆነውን የውሃ ሀብት ለማስተዳደር፣ ደህንነቱን ለመጠበቅ፣ ለመምራትና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት አስፈላጊ እንደሆነ አመላክተዋል።
መድረኩ እያንዳንዱ ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ ውኃ ማግኘት እንዲችል ወንዞች፣ ሐይቆች እና እርጥበታማ መሬቶች ሁሉ ደህንነታቸው ተጠብቆ ዘላቂነት ያለውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑንም አንስተዋል።
ውኃ አላቂ ሀብት እንደሆነና ጠብቆ በማቆየት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ መንከባከብ እና በጥበብ መምራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
እንደሀገር የውኃ ሃብት ልማት እና አስተዳደርን በማጠናከር ረገድ አስደናቂ እድገት እየታየ መሆኑን ገልጸው÷ በተፋሰስ ልማት አስተዳደር፣ በኃይድሮሜትሮሎጂ የመረጃ ስርዓትና በአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ፕሮግራሞች ላይ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ውኃ የቴክኒክ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊና ፖለቲካዊ ግዴታ መሆኑን በመረዳት እንደሀገር የተቀናጀ የውኃ ሀብት አስተዳደርን ማጠናከር እንደሚገባ መናገራቸውን በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ጌትነት ስሜ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!