ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱንም የሀዋሳ ከተማ የማሸነፊያ ግቦች ያሬድ ብሩክ አስቆጥሯል፡፡
ወላይታ ድቻን ከመሸነፍ ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ካርሎስ ዳምጠው ከመረብ አሳርፏል፡፡