ኪሊያን ምባፔ የወርቅ ጫማ ሽልማቱን ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ የ2024/25 የውድድር ዘመን የወርቅ ጫማ ሽልማቱን በዛሬው ዕለት ተረክቧል፡፡
ኪሊያን ምባፔ በ2024/25 የውድድር ዓመት 31 ግቦችን በማስቆጠር የስፔን ላሊጋ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ተጫዋቹ በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የወርቅ ጫማውን በማሸነፉ ደስተኛ መሆኑን ገልጾ ÷ በድጋሚ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡
የሪያል ማድሪድ ፕሬዚዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በበኩላቸው÷ ኪሊያን ምባፔ የክለቡ ስብስብ አካል በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የ26 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ አሁን ላይ በላሊጋው 11 ግቦችን በማስቆጠር የስፔን ላሊጋ ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃን እየመራ ይገኛል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
 
			 
				