Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ሰባት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት 12:00 ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ወደ በተርፍ ሙር ስታዲየም ከበርንሌይ ጋር የሚጫወት ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሰዓት ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር የሚጫወት ይሆናል።

እንዲሁም ብራይተን ሊድስ ዩናይትድን፣ ክሪስታል ፓላስ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳሉ።

የሊጉ ጨዋታ ምሽት 2:30 ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ቶተንሃም ሆትስፐር ቼልሲን ያስተናግዳል።

ምሽት 5:00 ደግሞ ያለፉትን አራት የሊጉን ተከታታይ ጨዋታዎች የተሸነፈው ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ በተቃራኒው ያለፉትን አራት የሊግ ጨዋታዎች በተከታታይ ማሸነፍ የቻለውን አስቶን ቪላን ይገጥማል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.