ማንቼስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ማንቼስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 በኢትሃድ ስታዲየም በሚካሄደው ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ባለፈው ሳምንት በአስቶንቪላ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ በሜዳው ይፋለማል፡፡
ሲቲዝኖቹ ባለፉት 9 የሊጉ ጨዋታዎች 16 ነጥብ በመሰብሰብ 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን ÷ የዛሬውን መርሐ ግብር በድል ካጠናቀቁ የሁለተኛነት ደረጃን መቆናጠጥ ይችላሉ፡፡
በውድድር ዓመቱ አስደናቂ ጉዞን እያደረገ የሚገኘው ቦርንማውዝ በበኩሉ 18 ነጥብ በመሰብሰብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በሌላ የሊጉ መርሐ ግብር 11 ሰዓት ላይ በለንደን ስታዲየም ዌስትሃም ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአቤል ነዋይ