የኦሊምፒክ ስፖርት የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት ያስችላል – አቶ ቀጄላ መርዳሳ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሊምፒክ ስፖርት የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት ያስችላል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፡፡
2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ ቀጄላ በዚህ ወቅት ÷ የኦሊምፒክ ስፖርት ከውድድር ባሻገር የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ÷ 2ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ በእድሜ ተገቢነት በኩል የተሻለ አፈጻጸም የታየበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ ለሀገር ማንሰራራት በሚል መሪ ሃሳብ ከጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በውድድሩ 12 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በ20 የስፖርት አይነት የተሳተፉ ሲሆን ÷ በአጠቃላይ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተወዳድረዋል፡፡
በውድድሩ በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚሳተፉ ስፖርተኞችን መምረጥ መቻሉ ተመላክቷል።
በዳዊት መሃሪ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!