መቻል ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአራተኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መቻል ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የመቻልን ግቦች መሐመድ አበራ እና ብሩክ ማርቆስ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥረዋል፡፡
መቻል በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ሲያሳካ፥ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እስካሁን አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም፡፡