Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ድቻ እና መቐለ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና መቐለ 70 እንደርታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታን ግቦች ቦና ዓሊ (በፍፁም ቅጣት ምት) እና ኪቲካ ጅማ አስቆጥረዋል፡፡

የወላይታ ድቻን የአቻነት ግቦች ደግሞ ምንተስኖት ተስፋዬ እና ካርሎስ ዳምጠው (በፍፁም ቅጣት ምት) ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን ነጥብ አሳክቷል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.