4ኛው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 4ኛውን የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል አስጀምረዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኤክስፖው የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ከዘርፉ አልሚዎች እንዲሁም ተመራማሪዎች ከነጋዴዎች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ ያስችላል፡፡
በገጸ ምድር እና በከርሰ ምድር የሚገኝ በርካታ የበለጸገ ማዕድን ያላት ኢትዮጵያ የነበራትን ሃብት በሚገባ ሳትጠቀም መቆየቷን አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ ግን የዘርፉን ስብራት በሚጠግን መልኩ በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
መንግስት ለማዕድን ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ÷ ከአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ማዕድን መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ለአብነትም ኢትዮጵያ በቅርቡ በ1ዐ ቢሊየን ዶላር የጀመረቻቸው የተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታዎችን ጠቅሰዋል፡፡
ኤክስፖው ከሕዳር 4 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ÷ በዚህም የዘርፉ አምራቾችና አቅራቢዎች ፣ የቴክኖሎጂ አምራቾችና አቅራቢዎች ተገናኝተው ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁ ይሆናል፡፡
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተገኝተዋል፡፡
በዓለምሰገድ አሳዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!