Fana: At a Speed of Life!

ክልሎች እምቅ የመልማት አቅማቸውን በሚገባ እየተጠቀሙ ነው – አፈ ጉባዔ አገኘሁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ከለውጡ ወዲህ ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል ያገኙ ክልሎች እምቅ የመልማት አቅማቸውን በሚገባ እየተጠቀሙ ነው አሉ።
አፈ ጉባዔው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የመሰረተ ልማት ሥራዎች አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የሆሳዕና ከተማን የኮሪደር ልማት፣ የተቋማት ማዕከላት ግንባታ እንዲሁም ለ20ኛው ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓሉ የሚከበርበትን ስታዲየም ተመልክተዋል፡፡
አፈ ጉባዔ አገኘሁ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ከለውጡ ወዲህ ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል ያገኙ ክልሎች እምቅ የመልማት አቅማቸውን በሚገባ እየተጠቀሙ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችም እምቅ አቅምን በሚገባ የመጠቀም ተግባርን ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል።
የለውጡ መንግስት ራስን በራስ ለማስተዳደር የነበሩ ጥያቄዎችን ከመመለስ ባሻገር የእውነተኛ ፌዴራሊዝምን መተግበር እንደሚያሳይ አውስተዋል፡፡
ክልሉ 20ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ለማስተናገድ እያደረገ ያለው ዝግጅት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡
በሰለሞን በየነ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.